13 October 2021

ሁለቱ እንቁ እህቶቻችን ሞሪን አቼንግ እና ደኒያ ጋይል ድጋፋችን ይገባቸዋል

 ሰሞኑን የተባበሩት መንግስታት ባልደረባ የሆኑት ሁለት አፍሪካውያን እህቶቻችን ከስራ ገበታቸው ላይ እንዲነሱ መወሰኑን ከመገናኛ ብዙሃን ሰምተናል። በተባበሩት መንግስታት ድርጊትም ማዘናችንን ብዙሃን ሶሻል ሚዲያ ላይ ገልፀናል። ቁጣችንን መግለፃችንን እየቀጠልን በተጓዳኝም እነዚህ ድንቅ የኢትዮጵያ ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ዘመቻችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን። 

እህቶቻችን ሞሪን አቼንግ እና ደኒያ ጋይል የተባበሩት መንግስታት ባልደረባ ቢሆኑም ድርጅቱ በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርገውን ተፅዕኖና ደባ ያጋለጡ ጀግኖች ናቸው። ሁለቱ እህቶቻችን ለህሊናቸው የቆሙ፤ ስለ እውነት የሞገቱና የታገሉ፤ ኢትዮጵያ ላይ የሚደረገው ደባ አግባብ አይደለም ያሉ፤ የየዘርፋቸው (IOM- Ethiopia & UNFPA Ethiopia ) የኢትዮጵያ ኃላፊዎች ቢሆኑም በወቅቱ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የነሱ ሃሳብ እንዳይካተት የታገዱ፤ ስለደባውም በቁጭት የተናገሩ ናቸው። እህቶቻችን የኢትዮጵያ ባለውለታዎች ናቸው። ለሀገራችን በፈታኝ ወቅት የደረሱ።
 

የተባበሩት መንግስታት ብዙ ፈተናዎች ያሉበት ድርጅት መሆኑ ግልፅ ነው። ድርጅቱ ዘረኝነት የተንሰራፋበትና የምዕራባውያን ጉዳይ ማስፈፀሚያ ድርጅት መሆኑን የዓለም ህብረተሰብ ያወቀው ነው። በተለይ ግን በኢትዮጵያ ላይ ያለው ገለልተኛ ያልሆነ አቋም እጅግ አሳሳቢ ነው። ስለዚህ ድርጅቱ ላይ የተቻለንን ያህል ዘመቻ በማድረግና ችግሮቹን በማጋለጥ ለውጥ እንዲያመጣ ግፊት ማድረጉን መቀጠል ያለብን ሲሆን፤ በተጓዳኘም ለኢትዮጵያ ካላቸው ቅን አመለካከት የተነሳ በድርጀቱ ኢትዮጵያ ላይ ደባ አይፈፀም ያሉ እህቶቻችን ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ በጋራ መታገል አለበን። ይህንን ትግል በተለይ በትዊተር ላይ በመሳተፍ በኩላችንን ዛሬውኑ እንወጣ።

ብዙ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሰሞኑን በትዊተር ላያ ካጋሩት መልዕክቶች ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተካተዋል።

Memorial Assembly for Neil Jameson - that is what he would have loved us to do!

In over 30 years of community organising, Neil Jameson organised and oversaw many assemblies. He enjoyed the drama, the razzmatazz, the stor...