25 February 2021

ሰገጤ ነኝ አለች ፤ እኔም ሰገጤ ነኝ

ሰገጤ ነኝ አለች

እኔም ተከተልኳት

እሷ ብቻ አይደለች

እኔም ሰገጤ ነኝ

ስለ ሀገር ማውራቷ

ከልብ መታከቷ

መጮህ መጨነቋ

ኢትዮጵያ ማለቷ

አንተን ካበሳጨህ

አንቺን ካናደደሽ

ችግሩ ካንተው ነው

ፈተናው ያንችው ነው

መድኃኒቱን እወቅ

መፍትሄ ፈልጊ

ሰገጤዎች ጎራ

ብዙ መፍትሄ አለ

ከመፍትሄው ዋናው

ወደርም የሌለው

የኢትዮጵያ ፍቅር

ፍቱን መድኃኒት ነው

 


ዲያስፖራው ለሀገሩ ፣ ኢትዮጵያን በጋራ ወደ ከፍታ

  የዲያስፖራ ኮሚኒቲዉ ወደ ሀገር ቤት በብዛት ለመግባት እየተዘጋጀ ባለበት በአሁኑ ወቅት ብዙ ነገሮችን ማሰብ ተገቢ ነው። ዲያስፖራው ወደ ሀገር ቤት መግባቱ በራ ሱ   ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታው ብዙ ነው...