4 April 2021

ከፊታችን የተደቀነውን ፈተና በጋራ ማለፍ ይገባል

የኢትዮጵያ ህዝብ በተለያየ ጊዜ ፈተናዎች አጋጥመውታል። ባለፉት 5 ወራት ግን ፈተናዎቹ ዘርፈ ብዙ ሆነዋል። ተደጋጋሚ ዘር ተኮር ጥቃቶች በትህነግ አነሳሽነት የተጀመረው ግጭትና ታላላቅ የሚባሉት እንደ ቢቢሲ እና ኤን ኤን ያሉ የሚዲያ ተቋማት የተዛባና እውነትን መሰረት ያላደረገ ዘገባ በሰብአዊ ድርጅት ስም የሚሰሩ እንደ አምነስቲና ሂውማን ራይትስ ዎች ያሉ ተቋማት ውስጥ ያሉ ድብቅ አላማ የተሸከሙ ግለሰቦችና ድርጅቶቹም ጭምር በግልፅ የሚታይ መርህ ያጣ ውንጀላ የአውሮፓ ህብረትና የአሜሪካ ቅጥ ያጣ ጉትጎታና ከልክ ያለፈ ጫና።


የኢትዮጵያ ጠላቶች ከዚህ የበለጠ ጫና ለመፍጠር ሊሞክሩ ይችላሉ። የሰው ኃይል የገንዘብና የቁሳቁስ አቅርቦት በማሟላት የበለጠ ጥፋት ለማስከተል 24 ሰዓታት ባለማቋረጥ ሊሰሩ ይችላሉ። ከምንም ጊዜ በላይ ጥንቃቄና አርቆ አስተዋይነት ያስፈልገናል:: ዛሬም እንደ ጥንቱ ተስፋ ያስፈልጋል። ከምንም በላይ አንድነት ያስፈልጋል።

እንደ ኢትዮጵያዊ ከመቼውም ጊዜ በላይ መደራጀትና ለአንድ አላማ መስራት ብቸኛው አማራጫችን ነው::

ከፊታችን የተደቀነው ፈተና መታለፉ አይቀርም። ፈተናዎቹ ቢበዙም ህዝባችን ዛሬም እንደ ጥንቱ በህብረት በመሆን ኢትዮጵያን ሊታደጋት ይገባል። ኢትዮጵያም ማሸነፏ አይቀርም።

በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውያን ከመቼውም በላይ በህብረትና በብዛት በመሆን ስለ ኢትዮጵያ ሊጮሁና ለኢትዮጵያ ህብረት በትጋት ሊሰሩ ይገባል። ኢትዮጵያ ከመቼውም በላይ ልጆቿን ትሻለች::ሀገራችን ስትጠራን ደግሞ አቤት ማለት ምርጫችን ሳይሆን ግዴታችን ነው። ይህንን ግዴታችንን ጊዜ ሳንወስድ መወጣት አለብን። ሀገራችን የገባችበትን አጣብቂኝ ሁኔታም በሰከነ አዕምሮ መመርመር የግድ ይሏል።

በውጩ ዓለም የምንኖር ሰዎች ብዙ ጊዜ የምንገነዘበው ነገር አለ። በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚኖረው ፍጥጫ እጅግ በጣም ከባድ መሆኑን። ፓርቲዎቹ እስከ መጨራሻው የሚነጋገሩ አይመስሉም። የሀገር ጉዳይ ሲመጣ ግል ሁሉም በአንድነት ይቆማሉ። በፖለቲካ አመለካከት መለያየት፤ በሀገር ጉዳይ ግን አንድ መሆን በየትኛውም አለም ያለ ነው። ኢትዮጵያውያንም በሀገር ጉዳይ ላይ ቁርጥ የሆነ አቋም ሊኖረንና ለወደፊቱ ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ልናስረክበው ይገባል።

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም።

The importance of small wins - Tiny changes, remarkable values!

  Reflecting on the book I once read, Atomic Habits, and also reflecting on my long Community Organising life, the importance of small wins ...