7 September 2018

ኢትዮጵያዬ የኔ ናፍቆት




ኢትዮጵያዬ የኔ ናፍቆት
ትውስ አልሽኝ እናት አለም

አውዳመቱ፣ ግርግሩ፣ 
ድርድሩ፣ ፉክክሩ
አንተ ትብስ 
አንቺ ትብሽ
ስንባባል የኖርንበት
እረ ስንቱ ኢትዮጵያዬ
ስንቱን ላንሳ፤ ስንቱን ጥዬ 
ከትዝታው፣ ከትውስታው

ልንገርሽ እናት አለም
ላጫውትሽ ኢትዮጵያዬ
በውስጤ የኖረውን

በጥቂቱ ልንገርሽ
ከታሪኬ ላካፍልሽ
ኢትዮጵያዬ ላውጋሽ
ትዝታዬን ላጫውትሽ

በአየር ክልልሽ ያለፍኩት 
በሰማይሽ ያቋረጥኩት 
አልረሳውም ኢትዮጵያዬ 
የተሰማኝን ስሜት
የነዘረኝን ንዝረት

የኢትዮጵያ አየር ክልል 
ውስጥ ነህ ቢለኝ ካርታው

ኢትዮጵያን እያለፍናት ነው 
ቢለኝ ያልገባው ጎረቤቴ
በመፅሃፍ ተደብቄ
ሥራ የበዛበት ሆኜበት 
እንባ እየተናነቀኝ
አንዲትም ቃል ትንፍሽ ሳልል
አለፍኩሽ እኮ ኢትዮጵያዬ::

ዛሬ ግን ኢትዮጵያዬ
አዎ ዛሬ ግን ሀገሬ 
የተስፋ ስንቄን ሰንቄያለሁ 
ብቅ ብዬም አይሻለሁ

የአቅሜንም ጀባ እላለሁ
ብድርሽንም እከፍላለሁ

ኢትዮጵያዬ እንገናኛለን 
ዳግምም እንተያያለን

ትናንት ኢትዮጵያዊ
ዛሬም ኢትዮጵያዊ
ነገም ኢትዮጵያዊ
ሁሌም ኢትዮጵያዊ
ኩሩው ኢትዮጵያዊ

እመጣና አይሻለሁ
የአቅሜንም ጀባ እላለሁ
ቃሌንም አከብራለሁ::

(ማስታወሻነቱ በስደት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን)


The Global Refugee Forum – time for meaningful participation of Refugees

  As the Global Refugee Forum takes place between 13 - 15 December 2023 in Switzerland, it is vital that we have meaningful participation of...