22 February 2019

ልማትም ሆነ ግንባታ ከሰብዓዊ መብት አይቀድምም


ሰሞኑን በለገጣፎ ብዙሃን ዜጎቻችን የመኖሪያ ቤቶቻቸው ፈርሰውባቸዋል። ዜጎች ሳይወዱ በግድ ወደ ጎዳና እንዲወጡ ተገደዋል። ይህ ክስተት እጅግ አሳዛኝና በጣምም አሳሳቢ ነው። ዜጎቻችንን ማዕከል ያላደረገ ልማት ምኑን ልማት ነው? የፈረሱትና ለመፍረስ እቅድ የተያዘላቸው ቤቶች ህገ ወጥ በሆነ መልኩ ተሰርተው ቢሆን እንኳ በምላሹ ዜጎች ለጎዳናና ለችግር መዳረግ የለባቸውም። ቤቶቹ የተሰሩት አስተዳደሩ እያየ ነው። ስለዚህ ችግሩ የነዋሪዎቹ ብቻ አይደለም። ጥፋትን በጥፋት ለማረም መሞከር ለማንም አይጠቅምም። የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራል መንግስት ለጉዳዩ ትኩርት ሰጥቶ ተገቢውን ምላሽ ሊሰጠው ይገባል። እቅድ በእቅድ ይሻራል። አዎ ሰው ያወጣውን እቅድ ሰው ሊሽረው ይችላል። ለችግሮች አማራጭ መፍትሄ ይፈለጋል እንጂ እኔ ብቻ ያልኩት መሆን ያለበት ካልን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። የእኔ ሃሳብ ብቻ ነው ትክክለኛ ሃሳብ ማለት አያዋጣም:: የመነጋገርና የመተማመን ባህል ሊዳብር ይገባል።

ባለፉት ወራት በሀገራችን ያየነው ለውጥ እጅግ አበረታች ነው። ይህንን ለውጥ ዘላቂ በማድረግ ዜጎቻችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ ሊሰራ የሚገባ ሲሆን ለስኬቱም የሁሉም ቀናና ሀገር ወዳድ ዜጋ ትብብርና ድጋፍ ከምንም በላይ ወሳኝ ነው። ለውጡን ለማደናቀፍ ሌት ተቀን ተግተው የሚሰሩ ግለሰቦችና ቡድኖች መኖራቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው። ስለዚህ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። በህይወት ዘመናችን ያገኘነውን መልካም አጋጣሚ ተጠቅመን ህዝብን ማዕከል ያደረገ ስራ መስራት ጠቀሜታው ለሁላችንም ነው።

Time to Get Out and Vote – Democracy in Action

  United Kingdom goes to the polls on July 4th.  Since the election was called by British Prime Minister Rishi Sunak, I have had the opportu...